የአድዋ ድል ምስጢር የነበሩት መተባበርና አንድነት ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ ትምህርት ይሰጣሉ

የአድዋ ድል ምስጢር የነበሩት መተባበርና አንድነት ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ ትምህርት ይሰጣሉ

አዲስ አበባ የካቲት 20/2010 የአድዋ ድል ምስጢር የነበሩት መተባበርና አንድነት አሁን በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት ትልቅ ትምህርት የሚሰጡ መሆናቸው ተገለጸ።
የአድዋ ድል ምስጢር የነበሩት መተባበርና አንድነት ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ ትምህርት ይሰጣሉ
የአድዋ ድል ምስጢር የነበሩት መተባበርና አንድነት ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ ትምህርት ይሰጣሉ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት 122ኛውን የአድዋ ድል በዓል ከተለያዩ የሙያ ማህበራትና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በፓናል ውይይት አክብሯል።

በውይይቱም የአድዋ ድልና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያላቸውን አንድነት የሚያትት ፅሁፍ ቀርቧል።

አድዋ ወራሪ ጠላትን ለመመከት ኢትዮጵያዊያንን በአንድነት እንዳዘመተ ሁሉ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብም ድህነትን ለማጥፋት በተከፈተው ዘመቻ ኢትዮጵያዊያን ከሊቅ አስከ ደቂቅ አሻራቸውን ለማኖር ያስቻለ ፕሮጀክት መሆኑ በፅሁፉ ተጠቁሟል።

ኢዜአ ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች እንዳሉት፤ አሁን ላይ ከኢትዮጵያዊያን እሴት ባፈነገጠ መልኩ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና መፈናቀሎች እየተስተዋሉ ነው።

እነዚህን ችግሮች በመፍታት ረገድ የአድዋ ድል ምስጢር የነበሩት መተባበርና አንድነት ትልቅ ትምህርት ይሰጣሉ ነው ያሉት።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ተማሪ ናትናኤል ስዩም "የአድዋን ጦርነት በአንድነት ድል እንዳደረግን ሁሉ የሚለዩን ነገሮች እንኳን ቢኖሩ በአንድነትና በመተባበር መፍታት ይገባል" ሲል ተናግሯል።

ተማሪ ናትናኤል በተለይ ምሁራን ማህበረሰቡን በትክክለኛው መንገድ የመምራት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር የኤዲቶሪያል ቦርድ አባል አቶ መስቀሉ ባልቻ በበኩላቸው ትውልዱ አድዋ ላይ የተሰራውን ስራ ተገንዝቦ ለአገር አንድነት ተቆርቋሪ መሆን እንዳለበት ነው የገለጹት።

ከኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር አውቅና ውጭ አሁን ላይ አንድነትን የሚሸረሽሩ መጻህፍት እየተበራከቱ መሆኑን የተናገሩት አቶ መስቀሉ "ትውልዱ በእነዚህ መጻህፍት ሃሳብ ተጽዕኖ ውስጥ እንዳይወድቅ ሊጠነቀቅ ይገባል" ብለዋል።

ወጣቱ ትውልድ እውነተኛ ማንነቱን አንዲያውቅ መንግስትና ማህበረሰቡ ብዙ መስራት እንዳለባቸው የተናገሩት ደግሞ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያ ሴቶች ማህበር የመጡት ወይዘሮ ተካሰች አሰፋ ናቸው።

ኃላፊነት በጎደለው መልኩ የተሳሳተ ታሪክ እየጻፉ ወጣቱን ወደ ግጭትና አለመግባባት የሚመሩ ሰዎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ቲያትር ባለሙያዎች ማህበር ስራ አመራር ኮሚቴ ጸሃፊ አቶ መላኩ አለማየሁ የአድዋ ድል "አገር ከራስ ጥቅም እንደሚበልጥ የታየበት ነው" ብለዋል።

"ድሉን ስንመረምር በልዩነት ውስጥ ሆነን አንድነትና መተባበር እናገኛለን" ያሉት አቶ መላኩ አሁን አየታዩ ያሉ ግጭቶችና መከፋፈሎች በቆዩ የአብሮነት እሴቶቻችን ላይ ጥላሸት የሚቀቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

"ሁሉም ኢትዮጵያዊ የአድዋን ድል ምስጢር በመገንዘብ፣ በመተባበርና በመተሳሰብ እሴት ችግሮችን በጋራ መፍታት ይገባዋል" ሲሉም አስገንዝበዋል።

Share on Google Plus

About ethinews

    Blogger Comment
    Facebook Comment

0 comments:

Post a Comment