ኢትዮጵያ ውስጥ ዜና : የኬንያ ፍርድ ቤት በርካታ ሶማሊያዊያንን ያስጠለለው የዳዳብ የስደተኞች ካምፕን ለመዝጋት የቀረበውን እቅድ ውድቅ አደረገ

የኬንያ ፍርድ ቤት በርካታ ሶማሊያዊያንን ያስጠለለው የዳዳብ የስደተኞች ካምፕን ለመዝጋት የቀረበውን እቅድ ውድቅ አደረገ – የኬንያ መንግስት በዓለማችን በትልቅነቱ የሚታወቀውን የዳዳብ የስደተኞችን ካምፕ ለመዝጋት ያቀረበው ሀሳብ በከፍተኛው ፍርድቤት ውድቅ ሆኖበታል፡፡
የዳዳብ የስደተኞች መጠለያ፥ ላለፉት 20 ዓመታት ከሶማሊያ የመጡ ስደተኞችን ሲያስጠልል የቆየ ነው።
ኬንያ ባለፈው ዓመት በርካታ ሶማሊያውያን ይኖሩበታል የሚባለውን የዳዳብ የሥደተኞች ካምፕን ለመዝጋት እቅድ ማቅረቧ ይታወቃል፡
በተለይም በተደጋጋሚ እያጋጠማት ያለውን የሽብር ጥቃት የሚፈጽሙት፥ በመጠለያው ያሉ የአልሻባብ አባላት ናቸው ከሚል መነሻ ነው የመዝጋት እቅዱን አቅርባ የነበረው።
ሆኖም የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባሳለፈው ውሳኔ፥ እቅዱ የኬንያን ህገመንግስት አንቀጽ 27 እና 28 የሚጥስ እንዲሁም የስደተኞችን መብት እናክብራቸውን ዝቅ የሚያደርግ ነው በሚል ተቃውሞታል፡፡
በዶናልድ ትራምፕ ውሳኔ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ በተባሉበት እና የኬንያ መንግስት ካምፑን ለመዝጋት በተቃረበበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ማሳለፉ በጦርነት እና በድርቅ ለተሰደዱት ሶማሊያውያን አፎይታን ይዞ መጥቷ እየተባለ ነው፡፡
ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም ውሳኔውን ደግፈውታል፡፡
የዳዳብ የስደተኞች የመጠለያ ካምፕ ከ260 ሺህ የማያንሱ ሶማሊያውያን ስደተኞችን በውስጡ ይዟል መባሉን ሲኤንኤንን ጠቅሶ የዘገበው ኤፍቢሲ ነው፡፡
Share on Google Plus

About ethinews

    Blogger Comment
    Facebook Comment

0 comments:

Post a Comment